"ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ " ያልኩት ጸጽቶኛል"
ጥያቄ፡ - ቃለ መሐላ በሚፈፅሙበት ጊዜ ዘላለማዊ ክብር ለጠ /ሚኒስትራችን ያሏት ቃል ብዙ ክርስቲያኖችን ያጠያየቀ ጉዳይ ሆናለች፡፡ ይህችን ቃል ሆን ብለው በርግጥም አምነውባት ነው ያሏት ወይስ የተፃፈልዎትን ነው ያነበቧት ?
ጠ /ሚኒስትር ኃ /መርያም፡ - (ትንሽ ካሰቡ በኋላ ) ያንን ንግግር ያዘጋጁት ንግግር አዘጋጆቹ ናቸው፡፡ ግን የንግግሩን ፅንሰ ሀሳብ መጀመሪያ እኔ ነኝ የሰጠኋቸው፡፡ እነሱ ቋንቋውን አሳምረው ቀናንሰውና ጨማምረውበት አሰካክተው ኤዲት አደርገው ከጨረሱ በኋላ እኔ ጋር ይደርሳል፡፡ እኔ ሀሳቤን በትክክል ይገልፃል የሚለውን አንኳሩን ክፍል ብቻ አይቼ ያቺን ቃል ሳላስተውል አመለጠችኝና እናም ምንም አማራጭ የለኝም አልኳት፡፡ ማታ ቤት ስመለስ ባለቤቴና ልጆቼ ሁሉ ገና ከበሩ ጀምሮ አተካራ ገጠሙኝ፡፡ ልጆቼ በተለይ የ 16 ዓመቷ ልጄ ያለችው አባ በምድር አላፊ የሆነ ስጋ ለባሽ ከኢየሱስ እኩል በላይ ክብር መውሰድ አይገባውም ብለህ ራስህ አስተምረህን የለም ብላ ስትለኝ በእውነት መልስ አጣሁ፡፡ ትንሽ ፈተና ገጥሞኝ ነበር እልሃለው
ጥያቄ፡ - እና ተፀፅተዋል ?
ጠ /ሚኒስትር ኃ /መርያም፡ - አዎን ... በኋላማ አስቀምጫቸው የሆነውን ነገር ሁሉ አስረድቼያቸው በጠረጴዛ ዙሪያ ሰላም ፈጠርን ፡፡ ግን አንድ ነገር ቤተሰቤም ሆነ መላ ክርስቲያን ወገኖቼ ይረዳሉ ብዬ ተስፋ የማድረገው ነገር እኔ የትናንት የትንሹ ኃ /ማሪያም ቤተሰብ አስተዳደሪና አንድ ተራ የሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን አባልና አማኝ ብሆንም ያንን ማንነቴን ምንም የሚቀይር ነገር የለም፡፡ ጌታ እስከፈቀደ አሁንም ወደ ፊትም ያን የትናንቱን አምላክ ማምለኬ እንደ ግለሰብነቴ ተጠብቆልኝ በአንፃሩ ደግሞ የ 80 ሚሊዮን ሕዝብ አደራና ኃላፊነት ስላለ የሁሉንም እመነት እና ኃይማኖት የማክበር ግዴታ አለብኝ፡፡ ሌሎቹም እንዲሁ የእኔን ኃይማኖት ለግሌ ነፃነቴን ትተውልኝ በመቻቻል ተያይዘን በወንድማማችነት በጋራ እንደምንኖር መገንዘብ አለባቸው፡፡ ግን ማንም ኃይማኖቱን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካዊም ሆነ ኃይማኖታዊ አድቫንቴጅ ለመውሰድ የማንንም ህሊና መጋፋት እንደሌለበት አምናለሁ፡፡

0 comments: